
ባሕር ዳር: ኅዳር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የጥቁር ሕዝቦች የታሪክ፣የቅርስና የትምህርት ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማዕከሉ ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ማድረጉ ኢትዮጵያ ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነት ላበረከተችው ጉልህ አስተዋጽኦ ዕውቅና የሚሰጥ ነው ብለዋል።
ጥቁር ሕዝቦች ታሪካቸውንና ባሕላቸውን ለማሳደግ በአንድነት እንዲሠሩ ፋይዳው የጎላ ነው ነዉ ብለዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን የሥራ ኀላፊዎች፣ የማዕከሉ መስራች አባላት፣ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮችና ሌሎች ተጋባዥ እግዶች መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!