የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

94

ባሕር ዳር: ኅዳር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ምደባን ይፋ አደረገ።

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የ”ሪሚዲያል” ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባቸውን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ተማሪዎች የተመደቡበት የትምህርት ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ”ሪሚዲያል” ፕሮግራሙን እንዲከታተሉም አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ የተማሪዎችን የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

ተማሪዎች የተመደቡበትን ተቋም ለመመልከት ከታች የቀረቡትን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ፡-

Website: http://Result.ethernet.edu.et

Telegram : https://t.me/moestudentbot

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ቀን ለማክበር ርእሳነ መሥተዳድሮችና ከንቲባዎች ጂግጂጋ ገቡ።
Next article“የብሩህ አዕምሮ ሽልማት ፕሮጀክት ለቀጣዮቹ 18 ዓመታት የሚቀጥል ነው” አድህኖ የተቀናጀ የገጠር ልማት ማኅበር