
ባሕር ዳር: ኅዳር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የተለያዩ ክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች እና የሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች ከንቲባዎች በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም ጂግጂጋ ከተማ ገብተዋል፡፡
ርእሳነ መሥተዳድሮቹና ከንቲባዎቹ ጂግጂጋ ሲገቡ የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!