በአማራ ክልል 13 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

37

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ እስከ ኅዳር 21/2016 ዓ.ም 12 ነጥብ 92 ቢሊየን ብር ሰብስቧል።

በክልሉ በ2016 የበጀት ዓመት በአጠቃላይ 71 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ከ12 ነጥብ 92 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል፡፡

የክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የታቀዱ ሥራዎች እንዳይስተጓጎሉ በሚተጉ ሠራተኞች፣ አመራሮችና ግብር ከፋዮች የጋራ ጥረት ከመደበኛ ገቢ ብር 11 ቢሊየን 992 ሚሊየን 702 ሺሕ 769 ብር እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር 932 ሚሊየን 965 ሺሕ 182 በድምሩ ከ12 ነጥብ 92 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article‘ዐፄዎቹ ከጦና ንቦቹ’ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ኾኗል።
Next article“በወጣቶች ማኅበራዊ ተሳትፎ እና በስፖርቱ ዘርፍ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል” የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ