ኢትዮጵያ በውኃ ዋና ስፖርት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡

40

ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በውኃ ዋና ስፖርት ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡

የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ስፖርት ብሔራዊ ቡድን በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 8ኛው የዞን 3 አፍሪካ ውኃ ዋና ሻምፒዮና በማስተርስ ዋና ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በዞን 3 የአፍሪካ ውኃ ዋና ሻምፒዮና ውድድር በታዳጊ ወጣቶች እና በማስተርስ ዋና ውድድር ተሳትፋ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ እና በ100 ሜትር ደረት ቀዘፋ በአትሌት እስከዳር አቻምየለህ አማካኝነት ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አስመዝግባለች፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ብቃት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር በስፖርቱ ዘርፍ እንሠራለን” የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
Next articleበአማራ ክልል የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ ለመሠብሠብ 26 ኮምባይነሮች ሥራ ላይ እንደሚገኙ ግብርና ቢሮ ገለጸ።