
ጎንደር: ኅዳር 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2016 ዓ.ም የዕቅድ ትውውቅ እንዲሁም የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን እየገመገመ ነው።
የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኅላፊ እርዚቅ ኢሳ በአካላዊ እና ሥነልቦናዊ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር በስፖርቱ ዘርፍ እንሠራለን ብለዋል።
የወጣቶች ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ለማስፋፋት ጅምር ተግባራት መኖራቸውን ያነሱት ቢሮ ኅላፊው በቀጣይም አዳዲስ የስፖርት ቤተሰቦችን ማፍራት ላይ በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።
በበጎፈቃድ አገልግሎት የወጣቶች ሚና ከፍተኛ በመኾኑ የበጋ በጎ ፈቃድ ሥራው ልክ እንደ ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ሁሉ በመደበኛነት ይቀጥላልም ብለዋል።
በውይይት ግምገማዉ:-
👉 የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን ግንባታ ለማጠናቀቅ ርብርብ ማድረግ እና መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት እንደሚገባ ተገልጿል።
👉 የተለያዩ የውድድር መድረኮችን ወደ ክልሉ በማምጣት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር ያስፈልጋልም ተብሏል።
👉 የመላው አማራ ጨዋታ፣ የታዳጊ ወጣቶች ምዘና፣ የሻምፒዮን እና የክለቦችን ውድድሮች ማካሄድ እንዲሁም መሰል ሥራዎች በጥንካሬ ተነስተዋል።
👉 የአካባቢ ፀጋዎችን በበቂ ሁኔታ አለመጠቀም
👉 የቴክኖሎጂ አቅርቦት ዝቅተኛ መኾን
👉የባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና ክትትል የተጠናከረ አለመኾን
👉ትኩረት የሚሹ ወጣቶች ፍትሐዊ ተጠቃሚ አለመኾናቸው በድክመት የተነሱ ናቸው።
በቀጣይም በድክመት የተነሱ ተግዳሮቶችን በማረም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እንደሚሠራ ተነስቷል።
ዘጋቢ፦ አዲስ ዓለማየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!