
ባሕር ዳር: ኅዳር 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዓሉ ዛሬ ህዳር 26/2016 ዓ.ም የብዝኃነት ቀን በሚል ስያሜ በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች በደማቅ ኹኔታ እንደሚከበር በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ አስታውቀዋል::
የበዓሉ አካል የኾነው የባሕል ኤግዚቢሽን ትናንት መከፈቱ ይታወሳል። የኢግዚቢሽኑ መከፈት በርካታ ዓላማዎች እንዳሉትም አቶ ተረፈ እንዲህ አብራርተዋል፡፡
📕 ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝኃነት ተምሳሌት መኾኗን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት ማሳየት
📕 የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ባሕልን በማስተዋወቅ የባሕል ልውውጥ እና የሕዝቦች ትስስርን ማጎልበት፤ እርስ በርስ እንዲተዋወቁ እድል መፍጠር
📕 ያደገ ትውውቅን በማረጋገጥ መቻቻልን፣ መከባበርን እና አብሮነትን ማረጋጥ
📕 ኅብረ-ብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት ግንባታን ማጎልበት
📕 ኢትዮጵያዊ ማንነት ማለት የሁሉም የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ማንነት፣ ባሕል እና እሴቶች ድምር ውጤት መኾኑን ማሳየት ናቸው ተብሏል።
ዘጋቢ፡- አብነት እስከዚያ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!