የንግድ ትርዒት እና ባዛር በጅግጅጋ ከተማ ተከፈተ።

52

ጅግጅጋ: ኅዳር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)18ኛውን የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በምታስተናግደው ጅግጅጋ የበዓሉ አካል የኾነው የንግድ ትርዒት እና ባዛር ተከፍቷል፡፡

በዓሉ ”ብዝኅነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ መልዕክት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦችን ባሕል እና እሴት የሚያንጸባርቁ የተለያዩ አልባሳት በንግድ ትርዒት እና ባዛሩ ላይ ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም ተኪ ምርቶች፣ የፋብሪካ እና የዕደ ጥበብ ውጤቶች እንዲኹም ሌሎች ግብዓቶች ለሸማቾች ቀርበዋል።

የንግድ ትርዒት እና ባዛሩ በአምራቾች፣ በአቅራቢዎች እና በሸማቾች መካከል የንግድ ትስስርን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተገልጿል።

ዘጋቢ፡- አብነት እስከዚያ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል በ14 ከተሞች የመሬት ምዝገባ (ካዳሥተር) ሥራ እየተሠራ መኾኑን መሬት ቢሮ ገለጸ።
Next articleዳር 15/2016 ም.አ ቺርቤዋ ጋዚቲ