“ኢንዱስትሪዎች ገበያ፣ ካፒታል፣ ብቁ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ሰላምም መሠረታዊ ጉዳይ ነው” የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለም

84

ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም ሚንስትሩ ብናልፍ አንዷለም በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘውን ካርቪኮ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘውና የስፖርት ትጥቅ ልብስን በማምረት ወደ አውሮፓ ገበያ የሚልከውን ካርቪኮ ኢትዮጵያ ፋብሪካ በሰላም ሚንስትሩ ብናልፍ አንዷለም በተመራ ልዑክ ተጎብኝቷል።

ካርቪኮ ኢትዮጵያ በሸድ ብዛትና በካፒታል አቅሙ ግዙፍ ፕሮጀክት መመልከታቸውን የተናገሩት አቶ ብናልፍ እንደነዚህ አይነት ፋብሪካዎች የውጭ ምንዛሬን በማምጣት ረገድ ሚናቸው የጎላ መኾኑን አብራርተዋል ።

ኢንዱስትሪዎች ገበያ ፣ካፒታል ፣ብቁ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ሰላምም መሠረታዊ ጉዳይ መኾኑን አንስተዋል። ሚኒስትሩ በሰሜኑ የሀገራችን ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱንም አስረድተዋል። አሁን ያለውን “ሰላም “ዘላቂ ለማድረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል።

በጉብኝቱ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሀመድአሚን የሱፍ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የጥናትና ምርምር ቢሮ ኃላፊ ተተካ በቀለ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ፈዲላ ቢያን ጨምሮ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ደራሽ ፈላጊ ወገኖች፤ በማጣት የተዘረጉ እጆች”
Next articleበአማራ ክልል በ14 ከተሞች የመሬት ምዝገባ (ካዳሥተር) ሥራ እየተሠራ መኾኑን መሬት ቢሮ ገለጸ።