
ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ የሚያጠናክረው መኾኑን የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።
በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ቻም ኡጋላ ኡሪያት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት አቀርበዋል ፡፡
አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ፕሬዝዳንት ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመሰረቱ 125 ዓመታትን ያስቆጠሩ ወዳጅ አገራት መኾናቸውን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሩሲያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በማድረግ የተለያዩ የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸው ግንኙነቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዳሻገረው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ደግሞ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!