“ማኅበረሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን” የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ

22

ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የ2016 ዓ.ም እቅድ ትውውቅና የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን በየደረጃው ካሉት የጤና ዘርፍ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በውይይቱ የተገኙት የቢሮው ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ በአማራ ክልል የሰላም እጦት ቢኖርም ማኅበረሰቡ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ እየተደረገ ነው ብለዋል። “ማኅበረሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን” ነው ያሉት

በጤናው ዘርፍ ያለውን ክፍተት በመሙላት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም በትኩረት መሥራት ይገባዋል ሲሉም አሳስበዋል።

በየደረጃው ያሉ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በክልሉ የገጠመው የጸጥታ ችግር ሳይበግራቸው ማኅበረሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ የጀመሩትን ሥራ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ኀላፊው መልእክት አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ: በቀለ ተሾመ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የልማት አጀንዳዎችን ስኬታማ ለማድረግ የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወሳኝ ነው” የአማራ ክልል አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን
Next article“ሪፖርተር ጋዜጣ በኅዳር 23 እትሙ በውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ለማድረግ መታቀዱን በማስመልከት ያወጣው ዘገባ ሃሰተኛ ነው” ብሔራዊ ባንክ