የተዘራውን ሐሰተኛ ትርክት በመንቀል የጋራ ትርክትን በመገንባት ኅብረ ብሔራዊት የኾነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ዝግጁ መኾናቸውን ሠልጣኝ የመንግሥት አመራሮች ተናገሩ።

39

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)አራተኛ ዙር የመንግሥት መሪዎች በጎንደር ከተማ ሥልጠና እየወሰዱ ነው። ከሥልጠናው ጎን ለጎን በከተማ አሥተዳደሩ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በከተማው አራት የተጎበኙ ታሪካዊና የልማት ሥራዎች ሲኖሩ ከዚህም ውስጥ የፀሃይ ሁለገብ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበራትን አንዱ ነው።

ሠልጣኞች በጉብኝታቸው የከተማውን ነዋሪ እንግዳ ተቀባይነት እንዳረጋገጡ ተናግረዋል። በልማት የተሠሩ መልካም ተግባራትን ለማየት እድል እንደፈጠረላቸውም ገልጸዋል።

ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ ያገኙትን ልምድ ተጠቅመው የሚያገለግሉትን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠሩ ሠልጣኞቹ ተናግረዋል።

የተዘራውን ሐሰተኛ ትርክት በመንቀል የጋራ ትርክትን በመገንባት ኅብረ ብሔራዊት የኾነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ዝግጁ ነን ብለዋል። በነበራቸው ቆይታም ደስተኞች እንደኾኑ ገልጸዋል።

በ4ኛው ዙር የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ሥልጠና እየተሳተፉ የሚገኙት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ ሲኾን ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል መሪ መልዕክት ሥልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

ዘጋቢ: ዳንኤል ወርቄ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር 9ሺህ 190 ኩንታል የማር ምርት ተሰበሰበ።
Next article“ኢትዮጵያ የአንድነት ሀገር ናት፤ የሚያምርባት እና የምትገለጥበት አንድነት እና ኅብረ ብሔራዊነት ነው” ሠልጣኞች