“ከግጭት የምናተርፈው ነገር ባለመኖሩ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት ይገባል” የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ

33

ደሴ: ኅዳር 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር በከተማው ከሚገኙ የቀጣና መሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። ከተማዋ ላይ ያለውን ሰላም ለማጠናከርና በየአካባቢው ማኅበረሰቡ ለሰላም መጠበቅ የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ ያለመ ውይይት ነው የተካሄደው።

ከተማዋ ሰላም የሰፈነባት እንድትኾን በየአካባቢው ከሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቅንጅት እየሠሩ እንደኾነ የቀጣና አስተባባሪዎች ተናግረዋል። አካባቢያቸውን መጠበቅ ከጀመሩ በኋላ ይደርስባቸው የነበረውን ዘረፋ ማስቀረት እና ሰላማቸውን መመለስ እንደቻሉ በውይይቱ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

የአማራ ሕዝብ ጥያቄ የደሴ ከተማ ማኅበረሰብም ጥያቄ ነው ያሉት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ “ከግጭት የምናተርፈው ነገር ባለመኖሩ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት ይገባል” ብለዋል። ሰላምን በማስጠበቅ እና የተጀመሩ የመሰረተ ልማቶችን በመጨረስ የከተማዋን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ማሻሻል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የኅብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በቁርጠኝነት እንዲሠራ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ ፦ ሰልሀዲን ሰይድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሕጻናት ትምህርት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት በጋራ መረባረብ ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)
Next articleበጎንደር ከተማ ሥልጠና እየወሰዱ ያሉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በከተማው ጉብኝት እያደረጉ ነው።