ፀደይ ባንክ በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

57

አዲስ አበባ: ኅዳር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፀደይ ባንክ በአማራ ክልል በዋግኽምራ እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጎል። የባንኩ ዋና ፕሬዚዳንት መኮንን የለውምወሰን ድጋፉ በአማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት በኩል ለተጎጂዎች አንዲደርስ አስረክበዋል።

የአመልድ ዋና ዳይሬክተር ዓለማየሁ ዋሴ (ዶ.ር) ከ450 ሺህ በላይ አስቸኳይ የዕለት ምግብ የሚፈልጉ ወገኖች ስለመኖራቸው ጠቁመዋል። በፀደይ ባንክ በኩል የቀረበው ድጋፉም አስፈላጊ በመሆኑ ባንኩን አመስግነዋል።
ዶክተር ዓለማየሁ ሌሎች ባንኮች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ባለሃብቶችም ድጋፍ በማድረግ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የክልሉን ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ችግሮች ለመፍታት ከተሜነት አይነተኛ መፍትሄ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)
Next article“በሕጻናት ትምህርት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት በጋራ መረባረብ ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)