
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሠራች ያለው ሥራ ለአፍሪካ ምሳሌ መሆን እንደሚችል የናይጀሪያ የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር አቡበከር ክያሪ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ እየተካሄደ ባለው ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ለዕይታ አቅርባለች።
የናይጄሪያ የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር አቡበከር ክያሪ ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ጎብኝተዋል። ሚኒስትሩ በጉብኝታቸውም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እያከናወነችው ያለው ተግባራት የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡
በኢትየጵያ እየተከናወነ ያለው የአረንጎዴ አሻራ ለናይጄሪያ ብሎም ለመላው አፍሪካ ምሳሌ መሆን ይችላልም ሲሉ ተናግረዋል። ናይጄሪያ የአረንጓዴ ልማት ላይ ተመሳሳይ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የጠቆሙት ሚነስትሩ፤ ኢትየጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያገኘችውን ይህን መሰል ውጤት ናይጄሪያ ልምድ መውሰድ ትፈልጋለች ብለዋል።
በመሆኑም ለዚህ የአረንጎዴ አሻራ ስኬት ሚስጥር ናይጄሪያ ወደ ኢትየጵያ በመምጣት ለመመልከት ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸው ሚኒስትሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!