
ባሕር ዳር: ኅዳር 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኮፕ28 ጉባኤ አስቀድሞ ከቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዴ ክሮ ጋር በኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ (ፓቪሊዮን) ተገናኝተዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በወቅታዊ የሀገር ውስጥ እና ሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!