“የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እኩልነታችንን፣ አንድነታችንን፣ ሀገራዊ ሰላማችንን እና መከባበራችንን ለዓለም የምናሳይበት ሊኾን ይገባል” የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አፈ ጉባኤ ፈንታይቱ ካሴ

54

ሰቆጣ: ኅዳር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) እኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን በሚል መሪ መልዕክት 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ እየተከበረ ነው።

በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክር ቤት እየተከበረ በሚገኘው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የፓናል ውይይት ላይ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ አፈ ጉባኤ ፈንታይቱ ካሴ ተገኝተዋል።

አፈ ጉባኤዋ “በዚህ ዓመት በሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እኩልነታችንን፣ አንድነታችንን፣ ሀገራዊ ሰላማችንን እና መከባበራችንን ለዓለም የምናሳይበት ሊኾን ይገባል” ብለዋል።

አፈጉባኤዋ እንደክልል የገጠመውን ችግር በሰላማዊ ውይይት መፍታት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በመርሐ ግብሩም የብሔረሰብ አሥተዳደሩ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ሀገራዊ ሰላምን ለማስቀጠል የሚረዱ ውይይቶች፣ የኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የሚያሳዩ ሙዚቃዎች እና የደም ልገሳ ሥራም ተከናውኗል።

በዓሉ እስከ ሕዳር 29/2016 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚከበር ከአሥተዳደር ምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሚወጡ ፖሊሲዎች እና ሕጎች የአካል ጉዳተኞችን መብት እና ጥቅም የሚያስከብሩ ይኾናሉ” ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ.ር)
Next article“ ተፈጥሮ የለገሰችው በረከት፣ ያልተነካው ሕብስት”