
አዲስ አበባ: ኅዳር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ግሎባል አሊያንስ ለኢትዮጵያውያን መብት ለጎንደር ዩኒቨርስቲ 15 ሚሊዮን ብር የሚገመት ለህክምና አገልግሎት የሚውል ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በርክክቡ ላይ ንግግር ያደረጉት የግሎባል አልያንስ ተወካይ በፈቃዱ ዓባይ የሕክምና መርጃ መሣሪያዎች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው መኾኑን ጠቅሰዋል። ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መኾኑንም ተናግረዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ.ር) የተደረገው ድጋፍ ለጎንደር ዩኒቨርስቲ አሥፈላጊ ነው፤
ለተደረገልን ድጋፍም ግሎባል አልያንስን እናመሠግናለን ብለዋል።
ዘጋቢ:- ራሔል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!