
ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽሕፈት ቤት ኀላፊ አደም ፋራህ በጎንደር የሥልጠና ማዕከል ተገኝተው የሥልጠናውን ሂደት ተመልክተዋል።
ሠልጣኞች በሥልጠናው የሚያገኙትን ግብዓት ተግባራዊ በማድረግ የሕዝቡን እርካታ በሚያረጋግጥ ሁኔታ በሰላም፣ በልማትና በመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ላይ በይበልጥ ውጤት ለማምጣት እንዲተጉ አሳስበዋል፡፡
ኀላፊው አያይዘውም ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ጉዟችንን ለማፋጠን ሀገራዊ ራዕይን በአግባቡ መገንዘብና ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡
የውስጠ ፓርቲ አንድነትን ማጠናከርና ተቋማዊ አቅምን ማጠናከር ለስኬታችን ድርሻው የጎላ መኾኑን የተናገሩት አቶ አደም እሳቤዎቻችንን የጋራ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሥልጠናው የአመራሩን አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚገነባ፣ ፓርቲንና መንግሥትን የሚያጠናክር መኾኑን ገልጸው የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከሠልጣኞች ጋር ውይይት ያደረጉት አቶ አደም ከሠልጣኞች የተነሱ ሃሳቦችን መነሻ በማድረግ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።
በመድረኩ ላይ የፌዴራል የክልል እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!