
ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)32ኛው የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በእውቀት የበለጸገ ዜጋ ለመፍጠር በትምህርት ዘርፉ የሚደረገው የማሻሻያ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ሚኒስትሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ የተሰራው ሥራ ያለንበትን ደረጃ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር ብለዋል።
በትምህርት ሥርዓቱ እየተደረገ ያለው ማሻሻያ ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር እድል የሚሰጥ ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ የተደረገው የማሻሻያ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!