
ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት አራት ወራት 193 ነጥብ 98 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የሚሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ከዓመት ዓመት እያደገ መጥቷል።
ከሐምሌ 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም ባሉት አራት ወራት 193 ነጥብ 98 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል ብለዋል።
ሚኒስትሯ በመግለጫቸው እንዳሉት ከተሰበሰበው ገቢ 129 ነጥብ 18 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ ታክስ የተገኘ ነው። 64 ነጥብ 79 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከቀረጥ እና ታክስ የተሰበሰበ እንደሆነም ተናግረዋል።
ገቢው ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ22 ነጥብ 74 በመቶ ብልጫ አለውም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!