ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በፆታዊ ጥቃት ላይ በሚመክረው መድረክ ለመካፈል ደቡብ አፍሪካ ገቡ።

72

ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም በሚመክረው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ገብተዋል፡፡

ጉባዔው ትናንት የተጀመረ ሲሆን እስከዛሬ እንደሚቀጥል በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል፡፡

በቦታው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር አብዱ (ዶ.ር) ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጉባዔ ያካፈሉት ተሞክሮ ኢትዮጵያ በለውጥ ተምሳሌትነት እንድትታይ ያስቻለ ነው” ቢልለኔ ስዩም
Next articleከበጋ መስኖ ልማት 40 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።