
ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በሶማሌ ክልል የሚካሄደውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ዝግጅትን ለመመልከት በአፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ ጂግጂጋ ገባ።
ልዑኩ ወደ ጂግጂጋ ያቀናው የ18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ቅድመ ዝግጅት ለመመልከት መኾኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ ገልጸዋል፡፡
የሶማሌ ክልል 18ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አስመልክቶ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን፣ የብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን አንድነት የሚያጠናክሩ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ተግባራትን እያከናወነ መኾኑንም ነው የገለጹት፡፡
በአፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራው ልዑክም ወደ ክልሉ የሄደው እነዚህን ተግባራት ለመመልከት ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት እንግዶችን ለመቀበል እና በዓሉን በድምቀት ለማክበር እያደረገ ያለው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ከተገመገመ በኋላ በቀሪ ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!