ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ድርጅት ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ።

59

ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ድርጅት ጉባኤ ላይ ንግግር አድረገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባኤ ላይ እንደ ክብር እንግዳ ባቀረቡት ቁልፍ ንግግር፤ የኢትዮጵያን ያለፉት አምስት አመታት የፓሊሲ ለውጥ፣ በብዝኃ ዘርፍ እድገት የተደረገ ኢንቬስትመንት፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ንፁህ የኃይል ምንጭ የተሰጠውን ትኩረት ብሎም ለማኅበራዊ ልማት ሥራ የተደረገውን አፅንዖት አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በዚህም ላይ ተመስርተው ሁሉን አካታች ለኾነ ዘላቂ የኢንደስትሪ ልማት ጥሪ ማቅረባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሁለገቡ የስፖርት ሰው ሕልፈት
Next article“በአማራ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት ተግባር እና ኀላፊነትን በአግባቡ መወጣት ይገባል” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ