በማኅበረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በየደረጃዉ እንደሚፈታ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ፡፡

30

ጎንደር፡ ኅዳር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ በ95 መድረኮች በማኅበረሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ባለድርሻ አካላት እና ተወካይ የማኅበረተሰብ ክፍሎች ተወያይተዋል፡፡

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ከዚህ ቀደም በተደረገ የቀጣና መድረክ 21 ሺህ የሚደርሱ የማኅበረተሰብ ክፍሎችን ማወያየት መቻሉን አስታዉሰዋል፡፡ በማኅበረሰቡ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካካል የጸጥታ፣ የመልካም አሥተዳደር፣ የሥራ እድል ፈጠራ እና መሰል ብልሹ አሠራሮችን ለመፍታት መሥራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በማኅበረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን በማኅበረሰቡ ለተወከሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ያቀረቡት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ ኀላፊ ፋሲል ሰንደቁ በከተማዉ የመሰረተ ልማት ሥራዎች ተጀምረዉ አለመጠናቀቅ በማኅበረተሰቡ ዘንድ ተደጋግመዉ ይነሳሉ ብለዋል። ለአብነትም የአዘዞ – ብልኮ መንግድ መጓተት እና በከተማው የንጹህ መጠት ዉኃ ፕሮጀክቶች አለመጠናቀቃቸዉ በከተማ አሥተዳዳሩ የሚፈቱ መኾናቸው ተጠቁሟል፡፡

ዜጎች ከቦታ ቦታ ተዘዋዉረዉ የመሥራት መብታቸዉ መነፈግ፣ በክልሉ ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች ድርቅ መከሰቱ ዜጎች ለረሃብ፣ ሞት እና መፈናቀል ተዳርገዋል፡፡ እነዚህ ደግሞ በፌደራል ደረጃ የሚፈቱ ተብለዉ ተለይተዋል ነዉ ያሉት።

ለወጣቶች ስፖርት ማዘዉተሪያ ስታዲየም አለመኖር፣ ሆስፒታሎች እና የጤና ተቋማት የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት፣ ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ አለመኖር ለሱስ እና አልባሌ ድርጊቶች እና ለችግር እያጋለጠ መኾኑ በማኅበረሰቡ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ናቸዉ ብለዋል።

በከተማዉ አላሥፈላጊ የጥይት ተኩስ እና የባጃጅ ላይ ስርቆት እና በተለምዶ ” ሃንግ ” የሚባለዉ ወንጀል ማስቀረት ያልተቻለበትን ምክንያት ተደጋግሞ መጠየቁን አንስተዋል።

የግብር ክፍያ ወቅቱን ያላገናዘበ ጭማሬ መኖር፣ ከቀን ወደ ቀን የኑሮ ዉድነት ማሻቀብ እና በከተማዉ የመሰረተ ልማት ስርቆት መኖር ፣ ሕገ ወጥ የቤት ግንባታ እና መሬት ወረራ፣ አመራር በጥቅማጥቅም እና በዘመድ አዝማድ መሾም የሚሉ ጥያቄዎች ተለይተዋልም ተብሏል።

በቀበሌ፣ በክፍለ ከተማ እና በመምሪያ ደረጃ የተነሱ ጥያቄዎችን ለይቶ በመያዝ በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ የሚፈቱትን ለይቶ በመያዝ መምሪያዉ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

የሚሠሩ መሰረተ ልማቶች ለማጠናቀቅ እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች ለመፈታት ማኅበረሰቡ ትልቁን ድርሻ የሚወስድ በመኾኑ ማኅበረሰቡን ማሳተፍ እንደሚያሥፈልግ ያነሱት ደግሞ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቻላቸዉ ዳኛዉ ናቸዉ።

ዘጋቢ፦ አዲስ አለማየሁ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሥራ አጥ ቁጥር መበራከት ለወንጀል መበራከት ምክንያት በመኾኑ አሁንም መፍትሄ እንደሚያሻው የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አባላት ተናገሩ፡፡
Next articleየሁለገቡ የስፖርት ሰው ሕልፈት