
ባሕር ዳር: ኅዳር 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 26ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎም ይጠበቃል። በጉባዔው የከተማ አሥተዳደሩ ተቋማትን የ2015 በጀት ዓመት አፈጻጸሞች ጥንካሬ እና ውስንነት ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል።
የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድም በምክር ቤቱ መደበኛ ጉባዔ ያጸድቃል ነው የተባለው።
በከተማዋ ውስጥ ያለውን የአከራይ ተከራይ ደንብ ማውጣትም ከምክር ቤቱ ጉባዔ አጀንዳዎች ውስጥ አንዱ ነው ተብሏል።
ዘጋቢ:- ዋሴ ባየ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!