የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የክሊንከር ሲሚንቶ ማምረቻ የመጨረሻ ፍሎር የመገጣጠሚያ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ።

107

ባሕር ዳር: ኅዳር 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የክሊንከር ሲሚንቶ ማምረቻ የመጨረሻ ፍሎር የመገጣጠሚያ እና የሮተሪ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግስ ግሩፕ ቦርድ ሊቀመንበር ብዙአየሁ ታደለ (ዶ.ር) በወቅቱ እንደተናገሩት የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የክሊንከር ሲሚንቶ ማምረቻ የመጨረሻ ፍሎር የመገጣጠሚያ እና የሮተሪ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ የሚገነባው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ከተጀመረ 11 ወራትን አስቆጥሯል። በዛሬው እለት በቀን 10 ሺህ ቶን ለማምረት የሚያስችለው የፕሪ ሂተር የመገጣጠሚያ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አበባው በቀል በሀገሪቱ ውስጥ እያደገ ያለው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ያጋጠመውን ከፍተኛ የኾነ የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል በቀን ከአስር ሺ ቶን በላይ ክሊንከር ማምረት የሚችል ነው ብለዋል።

ኢፕድ እንደዘገበው ፋብሪካው በመጀመሪያው ዙር በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ያመርታል ብለዋል ኢንጂነር አበባው። የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ስኬታማ ከሚያደርጉ የግል ዘርፎች መካከል የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ አንዱ እንደሚኾን ታምኖበታልም ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ተቋሙ ጭነት የማጓጓዝ አቅሙን ወደ ሁለት ሚሊዮን ቶን ከፍ አድርጓል” የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር
Next articleበኩር ጋዜጣ ኅዳር 17/2016 ዓ.ም ዕትም