“አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያነሷቸዉን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመፍታት በትኩረት እንሠራለን” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

44

ደብረ ብርሃን: ኅዳር 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የከተማ ልማት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ አሕመዲን ሙሐመድ(ዶ.ር) በደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ወደ ምርት የገቡ ኢንዱስትሪዎችን እና ግንባታቸዉ እየተፋጠነ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋዉረዉ ተመልክተዋል።

ኢንዱስትሪዉ ምቹ ኢንቨስትመንት የሚፈልግ በመኾኑ ከተንዛዛ የቢሮክራሲ አካሔድ እና ምላሽ የሚያላቅቅ ሥርዓትን በመዘርጋት የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን በማዘመን በኩል የክልሉ መንግሥት ትኩረት ሠጥቶ ይሠራል ብለዋል።

ኢንዱስትሪዉ የሚፈልጋቸው የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በመኖራቸዉ የሰዉ ኀይል ከማመቻቸት ጀምሮ ብዙ ሥራዎችን መሥራት ይጠይቃል ብለዋል።

በ10 ዓመት የልማት ስትራቴጂዎች ትኩረት ከተሰጣቸዉ መካከል የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት የክልሉ መንግሥት የተለያዩ አሠራሮችን በመዘርጋት እየሠራ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

ዶክተር አህመዲን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የጋራ ቤቶችን በመሥራት ኅብረተሰቡ ተጠቃሚ እያደረጉ የሚገኙትን ኢንዱስትሪዎችን የማበረታት ሥራ ይሠራል ብለዋል።

በደብረብርሃን ከተማ እና በሌሎች የክልሉ ሪጂዮፖሊታን ከተሞች ወደሥራ የገቡ መሰል ኢንዱስትሪዎችን የማሥፋት ሥራም በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

ዘመናዊ የዳታ ማእከል መሰረተ ልማት፣ የጥጥ ኢንዱስትሪ እና የፕላስቲክ እቃዎች መልሶ አገልግሎት ላይ ማዋል የሚችሉ ኢንዱስትሪዎች ከተጎበኙት መካካል ናቸው፡፡

ዘጋቢ፡- ሀብታሙ ዳኛቸዉ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበ13ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
Next article“ተቋሙ ጭነት የማጓጓዝ አቅሙን ወደ ሁለት ሚሊዮን ቶን ከፍ አድርጓል” የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር