
ባሕር ዳር: ኅዳር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሻንጋይ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሥራነሽ ይርጋ አሸንፋለች፡፡ አትሌቷ 2:21:28 በኾነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቃለች።
አትሌት ሥራነሽ ይርጋ ዳኜን በመከተል ኬንያዊቷ አትሌት ሴሊ ቼፕየጎ ካፕቲች 2:21:55 በኾነ ሰዓት በመግባት ሁለተኛ ኾና አጠናቅቃለች።
በወንዶች ኬኒያዊው አትሌት ፊሊሞን ኪፕቱ ኪፕቹምባ 2:05:35 በኾነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቅቋል። ታንዛኒያዊው አትሌት አልፎንስ ሲምቡ 2:05:39 በኾነ ሰዓት በመግባት በአራት ሰከንድ ልዩነት ውድድሩን ሁለተኛ ኾኖ አጠናቅቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!