
አዲስ አበባ: ኅዳር 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ ምዕራፍ፣ አዲስ ተስፋ ለአዲስ ክልል በሚል መሪ መልዕክት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጥቅምት 17/2016 በይፋ ተመስርቶ ወደሥራ መግባቱ የሚታወስ ነው። ክልሉ 10 ብሔር ብሔረሰቦችን ያቀፈ በ7 ዞኖች እና በ3 ልዩ ወረዳዎች የተዋቀረ ነው።
የሕዝቡን እና የልማት አጋሮችን አቅም በማቀናጀት የክልሉን ሕዝብ አጠቃላይ የልማት ፍላጎት ለማሟላት እና በሙሉ አቅሙ ለመሥራት እንዲያስችል ታስቦ ሀገር ዓቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ እንዲኹም የክልሉን ጸጋዎች ማስተዋወቂያ መድረክ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ዋና አፈ ጉባዔ ፋጤ ሰርሞሎ፣ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል፣ የልማት አጋሮች፣ የክልሉ ተወላጆች፣ የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!