
በ10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ መርሀ ግብር ዛሬ ሲካሄድ ደሴ ላይ ደሴ ከተማ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀንን 4 ለ0 አሸንፏል።
ደሴ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 14 ሲያሳድግ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን ደግሞ 7 ነጥብ ብቻ ይዞ ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛል፡፡
በሌላ የምድቡ መርሀ ግብር ጨዋታ ወልድያ በሜዳው በአቃቂ ቃሊቲ 1 ለ0 ተሸንፏል፡፡
አክሱም ከፌዴራል ፖሊስ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በአክሱም 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለገጠፎ ለገዳዲ ደግሞ ሶሎዳ አድዋን 1ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምድቡን ለገጠፎ ለገዳዲ በ22 ነጥብ ሲመራ ከአክሱም ጋር አንድ ቀሪ ጨዋታ የሚቀረው ወሎ ኮምቦልቻ በ17 ነጥብ ይከተላል፡፡ ወሎ ኮምቦልቻ ነገ በትግራይ ስታዲየም ከደደቢት ጋር የ10 ሳምንት መርሀ ግብሩን ያከናውናል፡፡
ዘጋቢ፦ ጀማል ይማም