
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር ውይይት በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ አደረጃጀት አማካሪ ይርጋ ሲሳይ እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው ተገኝተዋል። በውይይት መድረኩ ከ “እዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕስ በተለያዩ አካባቢዎች ሦስተኛ ዙር ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩ የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የክልሉን ወቅታዊ ጉዳዮች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች የሚመለከት ውይይት እየተደረገ ነዉ። በየደረጃዉ ንቃት ያለዉ የኅብረተሰብ ክፍል መፍጠር፤ ጽናት እና ቁርጠኝነት የተላበሰ የፖለቲካ እና የፀጥታ ኃይል መፍጠር ያስፈልጋል ተብሏል።
ክልሉ የገጠሙትን ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች መፍታት እና ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ወደ ቀያቸው መመለስ በምክክር መድረኩ ተነስተዋል።
ዘጋቢ፦ ሀዲስ ዓለማየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!