ክልል አቀፍና ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የደብረ ብርሃን ትምህርት መምሪያ እውቅና ሰጠ።

32

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍና የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን ተማሪዎች የደብረ ብርሃን ትምህርት መምሪያ እውቅና ሰጥቷል።

ከ8ኛ ክፍል ከሶሬሳ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማካይ ውጤት 95 በማምጣት የማርያም ወርቅ ጋሻው የ3 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላታል።

በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡት ደግሞ ከሚሊኒየም ትምህርት ቤት 613 ያስመዘገበው ተመሪ ዳግም ይባቤ ፣ ከሃይለ ማርያም ማሞ ትምህርት ቤት 611 በማምጣት ተማሪ ዮናስ አሰማኸኝ እና ከፊታውራሪ ገበየሁ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 605 በማምጣት ተማሪ ፋሲካ በዛወርቅ ከ10ሺህ ብር እስከ 8ሺህ ብር እንደየ ደረጃቸው ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱን የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማው ኮስትሬና ሌሎች አመራሮች ሰጥተዋል።

ዘጋቢ፦ ፈንታነሽ ሙሐመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልልን ወቅታዊ ጉዳዮች የሚዳስስ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ውይይት በአራት ማእከላት እየተካሄደ ነው።
Next articleጽናት እና ቁርጠኝነት የተላበሰ የፖለቲካ እና የፀጥታ ኃይል መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።