
ባሕር ዳር: ኅዳር 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከመላው ሀገሪቱ የተሰባሰቡት የጎንደር ማዕከል የመንግሥት አመራር ሠልጣኞች ሥልጠናቸውን ጀምረዋል፡፡
“ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው አራተኛው ዙር የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ሥልጠና እየተሰጠ ያለው፡
ሦስተኛ ዙር ሠልጣኞችን በፍቅር ተቀብላ በስኬት የሸኘችው ጎንደር አራተኛ ዙር ሠልጣኞችን ተቀብላ ማስተናገድ ጀምራለች፡፡
አራተኛው ዙር ሥልጠና ከኅዳር 14/2016 ዓ.ም እስከ ኅዳር 26/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 12 ቀናት ይሰጣል ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፡- እመቤት ሁነኛው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!