በ4ኛው ዙር የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚሳተፉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጎንደር ከተማ እየገቡ ነው።

38

ባሕር ዳር: ኅዳር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በ4ኛው ዙር የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚሳተፉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጎንደር ከተማ እየገቡ ነው። የጎንደር ሥልጠና ማዕከል አስተባባሪ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል(ዶ.ር) እና ሌሎች የክልል እና የከተማው የሥራ ኀላፊዎች በአፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሥልጠናው ከኅዳር 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 12 ቀን እንደሚሰጥ የጎንደር ሥልጠና ማዕከል አስተባባሪ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል(ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

በሥልጠናው ከ1 ሺህ 200 በላይ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እንደሚሳተፉ ዶክተር ወልደሚካኤል ተናግረዋል፡፡

ሠልጣኝ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠናውን በጎንደር የሥልጠና ማዕከል እንደሚወስዱ ተነግሯል።

ዘጋቢ፡- አገኘሁ አበባው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሥልጠናው የሰላምን አሥፈላጊነት በጉልህ የተረዳንበት ነው” ሠልጣኞች
Next article“ሰላማዊው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንደበፊቱ ሁሉም ዜጋ በሰላም የሚኖርበት ኾኖ እንዲቀጥል እንሠራለን” ርእሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ