“በአጎራባች ቀበሌዎች እና ወረዳዎች ላይ ያለው የሰላም እጦት ያሳስበናል” የለጋንቦ ወረዳ እና የአቀስታ ከተማ ነዋሪዎች

43

ደሴ: ኅዳር 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ አቀስታ ከተማ በወቅታዊ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ የዞኑ ኮማንድ ፓስት ሰብሳቢ ብርጋዴል ጀኔራል ዘውዱ ሰጣርጌ እና የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ጨምሮ የለጋምቦ ወረዳ እና አቀስታ ከተማ ነዋሪዎች እየተሳተፉበት ነው፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች አካባቢያችንን ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሰለፍ እናስጠብቃለን ብለዋል፡፡ መንግሥት ኅብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በቁርጠኝነት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንዲተገብር ጠይቀዋል።

ተወያዮቹ ለጋምቦ ወረዳ አብዛኛው አካባቢ እና የአቀስታ ከተማ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚገኝ ቢኾንም በአጎራባች ቀበሌዎች እና ወረዳዎች ያለው የሰላም እጦት ያሳስበናል ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ የሚያገኙት በሕግ እና በሥርዓት ብቻ መኾን አለበት ብለዋል። ውስጣዊ አንድነታችንን በመሸርሸር ለውጭ እና ለውስጥ ጠላቶቻችን በር መክፈትም ታሪካዊ ተወቃሽ እንደሚያደርግ አንስተዋል ተሳታፊዎቹ፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች እናስመልሳለን በሚል ሽፋን ኅብረተሰቡን ለእንግልት እና ለስቃይ መዳረግ የለበትምም ነው ያሉት።

ዘጋቢ፡- ጀማል ይማም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአዲስ የተመሰረተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዛሬ ሥራውን በይፋ ይጀምራል፡፡
Next article“ሥልጠናው የሰላምን አሥፈላጊነት በጉልህ የተረዳንበት ነው” ሠልጣኞች