
ባሕር ዳር: ሕዳር 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ የምሥራቅ ዕዝ አዛዥና የጎጃም ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ጽንፈኞቹ ፍላጎታቸውን በኀይል ለማሳካት የኢትዮጵያ ሕዝቦችን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን እየፈጸሙ በመሆኑ የመራዊ ሕዝብ ሊታገላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የሕግ የበላይነትን በሕገ ወጦች ላይ ለማስተግበር በሚደረገው ጥረት ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጎን የሰላም ኀይል በመሆን አካባቢውን እንዲያስከብርም አስገንዝበዋል፡፡
በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ሕዝቡ ከሠራዊቱ ጋር በአንድነት በመቆም ሊታገል ይገባል ብለዋል።
በዚህ ሕዝባዊ ውይይት ላይ፣ የኮር አዛዥ እና የሰሜን ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ብርጋዴር ጀኔራል አዲሱ መሐመድ፣ የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳዳሪ አሰፋ ጥላሁን እንዲሁም የመራዊ እና አካባቢው ሕዝብ ተሳትፈዋል፡፡
መረጃው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ ሚዲያ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!