“ትልቅ እምነት የተጣለበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የገንዘብ እና ሌሎችም ድጋፎች እናደርጋለን” የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች

49

ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት ናቸው። “በኢትዮጵያ እና እንግሊዝ መካከል ያለውን ትብብር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር እየተሠራ ነው” ሲሉም አምባሳደሩ ዳረን ዌልች ተናግረዋል።

እንደአምባሳደሩ ገለጻ በኢኮኖሚ፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የሀገራቱን ትብብር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር እየተሠራ ነው። ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ዕድገቷን እንድታረጋገጥ እና የመንግሥትን የሪፎርም አጀንዳ ለመደገፍ ሀገራቸው ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና ከዓለም ባንክ ጋር በቅርበት እየሠራች መኾኑንም ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር እንግሊዝ በኢትዮጵያ የጤና እና የትምህርት ሥርዓቱን ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎችን ለማጠናከር ድጋፍ እንደምታደርግም ተናግረዋል።

የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን ለማሳካትም ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ አጋርነቷን እንድምትቀጥልም አምባሳደር ዳረን ዌልች ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክርም ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ የሚያስችል ኹነኛ የሰላም መንገድ መኾኑን አንስተዋል። “ይህ ትልቅ እምነት የተጣለበት አካታች ሀገራዊ ምክክር እንዲሳካ የገንዘብ እና ሌሎችም ድጋፎች እናደርጋለን” ሲሉም ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደረሱ ሰብሎች ፈጥኖ መሰብሰብ እና የመስኖ ሥራዎችን ማስጀመር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደኾነ ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡
Next article“የማዘውተሪያ ስፍራ ባለመኖሩ አስፓልት ላይ ለመጫወት ተገድደናል” ወጣቶች