
ባሕር ዳር: ኅዳር 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የኩባ ምክትል ፕሬዝደንት ሳልቫዶር ቫልዴዝ ሜሳ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል::
ሁለቱ ወገኖች በሕክምና ዘርፍ፣ በቱሪዝም አገልግሎት፣ በትምህርት እና ስኳር ኢንደስትሪዎች ልማት የተጠናከረ ትብብር የሚኖርበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!