በጎንደር ከተማ የሚሠለጥሉ የመንግሥት አመራሮች ለአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት ጥገና የሚውል ድጋፍ አደረጉ።

35

ባሕር ዳር: ሕዳር 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ የሚሠለጥሉ የመንግሥት አመራሮች ለአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት ጥገና የሚውል ከ723 ሺህ ብር በላይ በእየግላቸው በማዋጣት ነው ድጋፍ ያደረጉት።

የአጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት የዓለም ሕዝብ ሀብት፣ የኢትዮጵያዊያን መኩሪያ ቅርስ ነው ያሉት ሠልጣኞቹ ድጋፉ ለቅርሱ ጥገና እንደሚውል ገልጸዋል።

ድጋፉንም ለከተማ አስተዳደሩ አስረክበዋል።

ዘጋቢ:–እመቤት ሁነኛው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሥራቸውን በመደበኛነት እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑ ተመላከተ፡፡
Next articleበሰሜን ወሎ ዞን የወባ በሽታ መቀስቀሱን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ።