
ባሕር ዳር: ኅዳር 11 /2016 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕርዳር ከተማ ሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
ሠልጣኝ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎቹ ከደሞዛቸው በማዋጣት ከ447 ሺህ ብር በላይ ነው ድጋፍ ያደረጉት። ድጋፉን የዲሞክረሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር መለሰ ዓለሙ ለርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ አስረክበዋል።
በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተ የዝናብ እጥረት ድርቅ ተከስቷል። በተከሰው ድርቅም 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን መግለፁ ይታወሳል።
በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!