
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሥልጠናቸውን ሲወስዱ የነበሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ስልጠና የማጠቃላያ ስነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው።
በማጠቃላያ ስነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ መክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን፣ በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅሕፈት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሚኒስትር መለስ ዓለሙን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ለቀናት በባሕር ዳር ከተማ ሥልጠና ሲወሰወዱ መቆየታቸው ይታወሳል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!