“ልምዶችን በመቀያየር የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ለውጤት ያበቃሉ” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

51

ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለሥራ ጉብኝት በጅማ ከተማ ተገኝተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ ወደ ከተማው ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ ከአማራ ክልል ፎገራ ወረዳ ልምድ በመቅሰም በጅማ ዞን እየለማ ያለው የሩዝ ምርት ተመልክተዋል። ልምዶችን በመቀያየር የሚሠሩ የልማት ሥራዎች ለውጤት እንደሚያበቁም ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል።

በጅማ ከተማ ውስጥ እየተሠሩ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ ልማቶችንም ተመልክተዋል። እንዲህ አይነት ልማቶች ከዘርፉ የገቢ ምንጭ ማግኘት እንደሚቻል ማሳያ እንደሆኑም ተናግረዋል።

በሌሎች ከተሞች የሚገኙ ወንዞችንም በዚህ አግባብ በማልማት የገቢ ማግኛ ማድረግ እንሠራለን ሲሉም ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግጭት የሚያጠፋው የሰውን ሕይወት፣ የሚበላው ኢኮኖሚን፣ የሚያቋርጠው ኢንቨስትመንትን ነው” ደሳለኝ ጣሰው
Next articleበኮምቦልቻ ከተማ የሳር መንደር የመኖሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ርእሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ መሐመድ በተገኙበት መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።