
ባሕር ዳር: ኅዳር 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በሞሮኮ በኤል-አብዲ ስታዲየም ከቡርኪና ፋሶ ጋር ጨዋታውን ያከናውናል።
በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ይጠቀማል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል። ቡርኪና ፋሶ ሙሉ ነጭ የሚለብሱ ይሆናል።
ጃሜህ ለሚን ከጋምቢያ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመራል። የሀገሩ ዜጎች ጃዎ አብዱልአዚዝ (ረዳት)፣ ዳርቦ ኦማር (ረዳት) እና ሳላህ ኦማር (አራተኛ) እንዲሁም አውዩ ዮሱፍ ከኡጋየንዳ በኮሚሽነርነት እንደተመደቡ ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!