የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት መሰብሰብ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።

51

ባሕርዳር: ኅዳር 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቅንጅታዊ አሠራርን በመተግበር የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት መሰብሰብ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አሳስቧል።

በቀጣዩቹ ደረቅና ፀሐያማ ቀናት አርሶ አደሮች፣ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የደረሱ ሰብሎችን በግዜ ሰብስበው በጥንቃቄ ወደ ጎተራ ማስገባት እንሚያስፈልግ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስገንዝቧል።

በኢትዮጵያ ሜቲዮሮሎጂ ኢንስቲቲዮት የትንበያ መረጃ መሰረት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ስለሚኖር ለመኸር ሰብል ምርት ተገቢውን ጥንቃቄ ካልተደረገ የምርት ብክነት ሊያስከትል እንደሚችም ተጠቁሟል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዕቅድ መሰረት የተፈጸሙ ቁልፍ ሥራዎችን በአግባቡ መለየት ያስፈልጋል” አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
Next article“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል” የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ.ር)