
ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2016 ዓ.ም ኢትዮጵያን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ዘርፍ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሚያደርጋትን ተቋም እውን ለማድረግ እየተሠራ ነው ሲል የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን አስቆጥሯል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ተቋሙ በነዚህ ዓመታት በርካታ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል።
ኢንስቲትዩቱ ከሚሠራቸው ዋና ዋና ሥራዎች አንዱ ኢትዮጵያን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሚያደርጋትን ተቋም እውን ማድረግ ነው ብለዋል።
ይህን ተቋም እውን ለማድረግም በዓለም ላይ በዘርፉ ተወዳዳሪ የሚያደርገው የዳታ ማስቀመጥ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!