
ጎንደር: ኅዳር 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ 3ኛውን ዙር ሀገር አቀፍ ሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙት የመንግሥት አመራሮች በከተማዋ የሚገኙ የኢንቨስትመንት እና የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
አመራሮቹ በጎንደር ብቅል ፋብሪካ በነበራቸው ጉብኝት እንዲህ ያሉ የልማት ሥራዎች አርሶ አደሩን ተጠቀሚ የሚያደርጉ እና አግሮ ኢንዱስትሪውን ለማጠራከር ያግዛሉ ብለዋል። ተሞክሮውንም በክልላቸው ለማስፋት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
በከተማዋ ባላቸው ቆይታ ያስተዋሉትን መልካም ገፅታ፣ የልማት እና ኢንቨስትመት ሥራዎች እንዲሁም የሕዝቡን እንግዳ ተቀባይነት ለማስተዋወቅ እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንደሚሠሩም ቃል ገብተዋል።
“ስለ ጎንደር ሰላም የሰማነው እና ተገኝተን ያረጋገጥነው ፈጽሞ አይገናኝም” ሲሉም ሠልጣኝ የመንግሥት አመራሮች በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ስለመኖሩ መስክረዋል። ጎንደር ብሎም መላው አማራ ክልል የተሟላ ሰላም እንዲያገኝ መላው ኢትዮጵያዊያን ከሕዝቡ ጎን ይቆማልም ብለዋል።
ዘጋቢ:- ቃልኪዳን ኃይሌ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!