“ሰላም ባለባቸው ወረዳዎች የመማር ማስተማር ሂደቱ በተገቢው መንገድ እየተካሄደ ነው” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ

27

ጎንደር፡ ኅዳር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ የትምህርት መምሪያ የሩብ ዓመት የሥራ ግምገማውን በጎንደር ከተማ እያካሄደ ነው።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ “ሰላም ባለባቸው ወረዳዎች የመማር ማስተማር ሂደቱ በተገቢው መንገድ እየተካሄደ ነው” ብለዋል።

የጸጥታ ችግር ውስጥ በቆዩ ወረዳዎችም የመማር ማስተማር ሥራውን ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ስለመኾኑ ጠቁመዋል።

በመድረኩ ያለፈውን ዓመት አፈጻጸም የሚያመላክት ሪፖርትም ቀርቧል። ጭልጋ፣ ታች አርማጭሆ እና ምዕራብ በለሣ በ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ተኛ ክፍል ፈተና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል።

የሁለተኛ ደረጃ መጻሕፍት እጥረት መኖሩ በውይይቱ ላይ ተነስቷል። መምሪያው ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በትብብር በመሥራት ችግሩን ለመቅረፍ በሂደት ላይ ስለመኾኑም ተጠቁሟል።

ዘጋቢ:- ተስፋየ አይጠገብ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleደካማ የሥራ ባሕል ችግር በሥራ እድል ፈጠራው ላይ ማነቆ እንደኾነበት የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር ገለጸ።
Next article“በሩብ ዓመቱ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 1ሺህ 200 ባለሃብቶች ፍቃድ አግኝተዋል” የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ