ደካማ የሥራ ባሕል ችግር በሥራ እድል ፈጠራው ላይ ማነቆ እንደኾነበት የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር ገለጸ።

26

አዲስ አበባ: ኅዳር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከግለሰብ እስከ ማኅበረሰብ ስር የሰደደው ደካማ የሥራ ባሕል ችግር በሥራ እድል ፈጠራው ላይ ማነቆ እንደሆነበት የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ ይሄንን ችግር ለመቅረፍ ከግንዛቤ ፈጠራ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መኾኑን ገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸሙን ከክልል ከተማ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል እየገመገመ ነው።

የሥራና ክሕሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በዚህ ሩብ ዓመት ለ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል። ሚኒስትሯ የተሻለ የሥራ ባሕል ለማስረጽ በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተሻለ ሰላም በመኖሩ የልማት ሥራዎችን እየሠራን ነው” የቀብሪደሃር ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር አብዱረዛቅ አወል
Next article“ሰላም ባለባቸው ወረዳዎች የመማር ማስተማር ሂደቱ በተገቢው መንገድ እየተካሄደ ነው” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ