“የተሻለ ሰላም በመኖሩ የልማት ሥራዎችን እየሠራን ነው” የቀብሪደሃር ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር አብዱረዛቅ አወል

27

ጅግጅጋ: ኅዳር 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቀደምት ከተማ የኾነችው ቀብሪደሃር ሰላም የሌላት አካባቢ ነበረች፤ አሁን ግን የተሻለ ሰላም አለ ሲሉ የከተማዋ ከንቲባ ኢንጅነር አብዱረዛቅ አወል ተናግረዋል። ይህንን ተከትሎ የትምህር፣ የመንገድ ፣ የአረንጓዴ ልማት እና መሰል የልማት ሥራዎችን ማከናወን ተችሏል ነው ያሉት።

ከተማ አስተዳደሩ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና የመናፈሻ አረንጓዴ ቦታዎችን በስፋት ማልማት መቻሉን ተናግረዋል። ከተማዋን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንድታገኝ መደረጉንም አንስተዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠው ልማቱ ቀጣይነት እንዲኖረው እና በሁሉም መስኮች እድገት እንዲታይ ህዝቡ ከመንግሥት ጋር በመኾን ጠንክሮ እየሠራ ስለመኾኑ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:-ድልነሳ መንግስቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአቢሲንያ ባንክ አጠቃላይ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን 158 ነጥብ 53 ቢሊዮን ብር ማድረሱን ገለጸ።
Next articleደካማ የሥራ ባሕል ችግር በሥራ እድል ፈጠራው ላይ ማነቆ እንደኾነበት የሥራና ክሕሎት ሚኒስቴር ገለጸ።